Hepatitis B Foundation President Dr. Chari Cohen is quoted in a powerful new story about hepatitis B in The New Yorker. You can read it here.

ከሄፓታይተስ ቢ ጋር መኖር 

ከያዘኝ ሄፓታይተስ ቢ መዳን እችላለሁ?

እንደ አዲስ የተያዙት አብዛኞቹ ጎልማሶች ያለምንም ችግር ይፈወሳሉ፡፡ ነገር ግን ህፃናት እና ታዳጊዎች ቫይረሱን ስኬታማ በሆነ መልኩ ማስወገድ አይችሉም፡፡

  • ጎልማሶች– 90% የሚሆኑት ጤናማ ጎልማሶች ቫይረሱን በማስወገድ ያለምንም ችግር ሲፈወሱ፤ 10% የሚሆኑት ስር በሰደደ የሄፓታተስ ቢ ተይዘዋል.
  • ታዳጊ ህፃናት– እድሜያቸው በ1 እና በ5 ዓመት ከሆናቸው መካከል እስከ 50% የሚሆኑት ታዳጊ ህፃናት ስር በሰደደው የሄፓታይተስ ቢ ተጠቅተዋል፡፡
  • ጨቅላ ህፃናት– 90% የሚሆኑት በከፍተኛ ደረጃ ሲጠቁ፤ 10% የሚጠጉት ብቻ ቫይረሱ ከሰውነታቸው ይወገዳል፡፡


"በጀማሪ" እና "ስር በሰደደ" ሄፓታይተስ ቢ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

በሄፓታይተስ ቢ መያዝ "በመጀመሪያ ደረጃ" ላይ እንዳለ ተደርጎ የሚወሰደው ግለሰቡ ለቫይረሱ ከተጋለጠበት ጀምሮ ያሉት የመጀመሪያ 6 ወራትን ያካትታል፡፡ ከሄፓታይተስ ቢ መያዝ ለመዳን የሚወስደው ጊዜ በአማካይ ነው፡፡ 

ከ6 ወራት በኋላ ውጤትዎ የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ እንዳለ (HBsAg+) ካሳየ "ስር የሰደደ" ሄፓታይተስ ቢ እስከ እድሜ ዘመንዎ አብሮ እንደሚቆይ ያረጋግጣል፡፡ 


በመጀመሪያ ደረጃ ላይ ያለ የሄፓታይተስ ቢ ካለብኝ ልታመም እላለሁ?

ሄፓታይተስ ቢ "ድምፅ አልባው በካይ” ይባላል፤ ለዚህም ምክንያቱ አልፎ አልፎ ምንም አይነት የበሽታው ምልክቶች አለመታየታቸው ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ጤናማ እንደሆኑ ያስባሉ፤ በቫይረሱ ስለመያዛቸው አያውቁም፤ ይህም ማለት ባለማወቅ ወደ ሌሎች ሰዎች ያስተላልፋሉ ማለት ነው፡፡ ሌሎች ሰዎች የተወሰኑ ምልክቶች ማለትም እንደ ትኩሳት፣ ድካም፣ የመገጣጠሚያ እና ጡንቻ ህመም፣ የምግብ ፍላጎት ማጣትን ተከትሎ ወባ እንደሆነ ይገምታሉ፡፡ 

ብዙም የማይስተዋል ነገር ግን ጠንከር ያሉ ምልክቶች የሚያካትቱት የበዛ ንፍጥ፣ ማስመለስ፣ የአይንና ቆዳ ቢጫ መሆን (ጁአንዳይስ የሚባለው) እና የጨጓራ መነፋት ሲሆን እነዚህ ምልክቶች የታየበት በፍጥነት የሀኪም እርዳታ ማግኘት ያለበት ሲሆን ግለሰቡም ወደ በሆስፒታል እርዳታ ማግኘት አለበት፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ ካለ የሄፓታይተስ ቢ መዳኔን እንዴት ነው ላውቅ የምችለው?

ያንተ ዶክተር ባደረገልህ የደም ምርመራ ቫይረሱ ከሰውነትህ እንደወጣና ሰውነትህ ተከላካይ አንቲቦዲ (HBsAb+) እንደፈጠረ ካረጋገጠ ወደፊት ሊገጥምህ ከሚችል የሄፓታይተስ ቢ የተጠበቅክ ከመሆንህም በተጨማሪ ወደሌሎችም አታስተላልፍም፡፡


ስር የሰደደው ሄፓታይተስ ቢ በደሜ ከተገኘምንድን ነው ማድረግ ያለብኝ?

ከ6 ወር በኋላ ባለው ጊዜ በተደረገ ምርመራ የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ መኖሩ ከተረጋገጠ ስር በሰደደው የሄፓታይተስ ቢ መያዝህን ያመላክታል፡፡ ከሄፓቶሎጂስት (የጉበት ስፔሻሊስት)፣ ከጋስትሮኢንተሮሎጂስት ወይም ስለ ሄታይተስ ቢ ከሚያውቅ የቤተሰብ ዶክተር ጋር ቀጠሮ መያዝ አለብዎት፡፡ ዶክተሩም የደም ምርመራ እንዲደረግ ሊያዝ፣ ምናልባትም የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ምን ያህል በጉበት ውስጥ እየተዛመተ እንዳለ ለማወቅና የጉበትዎን ጤንነት ለመፈተሽ የጉበት አልትራሳውንድ ሊያዝም ይችላል፡፡ ዶክተርዎ ሄፓታይተስ ቢ ያለበትን ደረጃ ለማየት እና ከህክምናው ምን ያህል እንደጠቀሙ ለማየት በዓመት ውስጥ ቢያንስ አንዴ አሊያም ሁለት ጊዜ ሊያይዎት ይገባል፡፡

ሁሉም በፀና የታመሙ ሰዎች ህክምና ጀመሩም አልጀመሩም በዓመት ቢያንስ አንድ ግዜ (ወይም ደጋግመው) ወጥነት ላለው የህክምና ክትትል በዶክተሮቻቸው መታየት አለባቸው፡፡ ምንም እንኳን ቫይረሱ ደካማ በሚባል ደረጃ ላይ ያለ ከሆነና ትንሽ ወይም ምንም ጉዳት የማያመጣ ከሆነ፤ ይህ በጊዜ ሂደት ስለሚለወጥ ወጥነት ያለው ክትትል ያስፈልጋል፡፡

ብዙ ሰር በሰደደ የሄፓታይተስ ቢ የተያዙ ሰዎች ጤናማ ሆነው ብዙ አመታትን መኖር ይመኛሉ፡፡ ስር የሰደደው ሄፓታይተስ ቢ እንዳለብዎ ከታወቀ፣ ቫይረሱ በደምዎ ውስጥ ለረዥም አመታት አብሮ ይኖራል፡፡ የህመም ስሜት ባይሰማዎት እንኳን፣ ቫይረሱን ወደሌሎች ሊያስተላልፉ እንደሚችሉ ማወቁ ጠቃሚ ነው፡፡ ተጠጋግተው የሚኖሩ ሰዎችና የወሲብ ጓደኞች ለሄፓታይተስ ቢ መከተባቸውን እርግጠኛ መሆን ጠቃሚ ነው የሚባለው ለዚህ ነው፡፡

 

የእኔን ሄፓታይተስ ቢ ለመቆጣጠር የሚረዳኝ የትኛው ምርመራ ነው?

ሄፓታይተስ ቢ ን ለመመርመር በዶክተሮች በብዛት ጥቅም ላይ የሚውሉት የምርመራ ኣይነቶች ሄፓታይተስ ቢ የደም ፓነል፣ ጉበት መስራቱን የሚያረጋግጥ ምርመራዎች (ALT፣ AST)፣ ሄፓታይተስ ቢ e-Antigen (HBeAg)፣ ሄፓታይተስ ቢe-Antibody (HBeAb) ፣ ሄፓታይተስ ቢ DNA quantification (ቫይራል ሎድ)፣ እና የጉበትን ገፅታ መመርመር (አልትራሳውንድ፣ ፊብሮስካን [ትራንሳይንት ኢላስቶግራፊ] ወይም ሲቲ ስካን)፡፡


ስር ለሰደደ ሄፓታይተስ ቢ መድሀኒት አለ?

እስካሁን ስር ለሰደደ ሄፓታይተስ ቢ የሚሆን መድሀኒት የለም፤ ነገር ግን መልካም የሚባለው ዜና በፅኑ የታመመውን ግለሰብ የጉበት ህመም እንዳይባባስ ቫይረሶቹ እንዲዳከሙ የሚያደርጉ ህክምናዎች አሉ፡፡ የሚራቡት የሄፓታይተስ ቢ ቫይረሶች ቁጥር በቀነሰ ጊዜ በጉበት ላይ የሚደርሰው ጉዳትም ይቀንሳል፡፡ ብዙም የተለመደ ባይሆንም እነዚህ መድሀኒቶች ቫይረሱን ሲያስወግዱ ይታያሉ፡፡ 

ያሉት ተስፋ ሰጪ ምርምሮች ሲታዩ፣ ወደፊት ስር የሰደደውን ሄፓታይተስ ቢ ለማከም የመረዱ መድሀኒቶች እንደሚገኙ ታላቅ ተስፋ አለ፡፡ የእኛን ጎብኙ መድሀኒት ተመልከቱ በመምጣት ላይ ያሉት ሌሎች ተስፋ ሰጪ መድሀኒቶች ዝርዝር፡፡


ስር የሰደደውን ሄፓታይተስ ቢ ለማከም የሚረዱ የተረጋገጡ መድሀኒቶች አሉ?

ሄፓታይተስ ቢ ን ለማከም የሚረዱት የአሁኖቹ መድሀኒቶች በጥቅሉ በሁለት የሚከፈሉ ሲሆኑ እነሱም አንቲቫይራል እና ኢሚዩን ሞዱሌተርስ ይባላሉ፦  

አንቲቫይራል መድሀኒቶች - እነዚህ መድሀኒቶች የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስን የሚያዳክሙ ወይም የሚያስቆሙ ብሎም የጉበትን መቃጠልና መጎዳት የሚቀንሱ ናቸው፡፡ እነዚህ በፒል መልስ ቢያንስ ለ 1 ዓመትና ከዚያም በላይ በቀን አንድ ግዜ የሚወሰዱ ናቸው፡፡ የአሜሪካው ኤፍ.ዲ.ኤ ያረጋገጣቸው 6 አንቲቫይራሎች ያሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ሶስቱ በቀዳሚነት የተቀመጡት አንቲቫይራሎች ለህክምና ይመከራሉ፡፡ እነሱም ቲኖፎቪር ዲሶፕሮክሲል (ቪሬድ/ቲ.ዴ.ኤፍ)፣ ቲኖፎቪርአላፈናማይድ (ቬምሊዲ/ቲ.ኤ.ኤፍ) እና ኢንትካቪር (ባራክሉድ)፡፡ መጀመሪያው መስመር ላይ ያሉት አንቲቫይራሎች አስተማማኝና በጣም ውጤታማ በመሆናቸው ይመከራሉ፡፡ በበሽታው ላይ ተፅዕኖ በማድረስም ከአሮጌዎቹ አንቲቫይራል የተሻለ ፕሮፋይል ያላቸው ሲሆን በታዘዘው መሰረት ከተወሰዱበሽታው በቀላሉ ሊላመዳቸው አይችልም፡፡ መድሀኒቱን መላመድ እያደገ ከመጣ ቫይረሱን ለማከምና ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ይሆናል፡፡

ኢሙዩኖሞዱሌተር መድሀኒቶች - እነዚህ መድሀኒቶች የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስን ለመቆጣጠር የሚረዳው የሰውነት የመከላከል አቅም እንዲያድግ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ ከ 6 ወር እስከ 1 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ በመርፌ የሚሰጡ ናቸው፡፡ በብዛት የታዘዘው ኢንተርፌሮን አልፋ-2b (Intron A) እናፔጊሌትድ ኢንተርፌሮን (Pegasys) ናቸው፡፡ በሄፓታይተስ ዴልታ ለተጎዱ ሰዎች ይህ በብቸኝነት የሚታዘዝ ህክምና ነው፡፡

 

እነዚህ መድሀኒቶች ስር ለሰደደ የሄፓታይተስ ቢ በሽታ "ፈውስ" ይሰጣሉ?

ምንም እንኳን የተሟላ ፈውስ ባይሰጡም አሁን ላይ ያሉ መድሀኒቶች ቫይረሱን በማዳከም በቀጣይ ጊዜያት የከፋ የጉበት በሽታ የመያዝ ስጋትን ይቀንሳሉ፡፡ በጥቂት ወራት ውስጥ ህመምተኛው የተሻለ ስሜት ይሰማዋል፤ ምክንያቱም ጉበቱ ላይ በቫይረሱ እየደረሰበት የነበረው ጉዳት እየቀነሰ ይመጣል፤ አሊያም ለረዥም ጊዜ ሲወሰድ ድጋሚ ሊያገረሽም ይችላል፡፡ አንቲቫይራል ዝም ብሎ የሚወሰድ አሊያም የሚቆም አይደለም፤ ለዚያም ነው ስለ ሄፓታይተስ ቢ ን እውቀት ያለው ዶክተር ስር በሰደደው የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ላይ ክትትል አድርጎ ህክምናውን ይጀምር የሚባለው፡፡

ስር በሰደደ የሄፓታይተስ ቢ መያዜ ቢታወቅ መድሀኒት መውሰድ አለብኝ ማለት ነው?

ማንኛውም ስር የሰደደ ሔፓታይተስ ቢ ያለበት ሰው ሁሉ መድሀኒት የማይወስድ መሆኑ ከግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ጠቃሚ ነው፡፡ መድሀኒት ለመውሰድ ብቁ ስለመሆን አለመሆንህ ለማወቅ ዶክተርህን ማነጋገር አለብህ፡፡ እርስዎ አሊያም የእርስዎ ዶክተር ህክምና መጀመር እንዳለብዎት ወሰናችሁም አልወሰናችሁም፣ በጉበት ሴፔሻሊስት ወይም ስለ ሄፓታይተስ ቢ እውቀቱ ባለው ዶክተር አዘውትረው መታየት አለብዎት፡፡

ለሄፓታይተስ ቢ ከእፀዋት የተዘጋጁ መድሀኒቶችን መጠቀም አስተማማኝ ነው?

በርካታ ሰዎች በሽታ የመከላከል አቅማቸውን ከፍ ለማድረግ ብሎም ጉበታቸውን ለማገዝ ከእፀዋት የተዘጋጁ መድሀኒቶችን ይጠቀማሉ፡፡ ችግሩ ያለው እነዚህን ምርቶች የሚያመርቱ ካምፓኒዎች ላይ የሚደረግ ቁጥጥር የለም፤ ይህም ጠንካራና አስተማማኝ የሆነ ምርምር እንዳይኖር አድርጓል፡፡ ስለሆነምየዕፀዋቱ ወይም ቫይታሚኑ ጥራት ከጠርሙስ ወደ ጡርሙስ የተለያየ ነው፡፡ ለሄፓታይተስ ቢ ተብሎ ከሚታዘዙ መድሀኒቶች ጎን ሌሎች ባህላዊ መድሀኒቶችን መጠቀም ጉበትን ለከፋ ጉዳት ይዳርጋል፡፡ እነዚህ ባህላዊ መድሀኒቶች ስር የሰደደ የሄፓታይተስ ቢ በሽታን አያክሙም፡፡

በኢንተርኔት እና በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስለ ምርታቸው የሚዋሹ ድርጅቶች ብዙ ናቸው፡፡ በፌስ ቡክ የኦንላይን ግዙን ጥያቄዎች እና የህሙማን ምስጋናዎች የውሸት ናቸው፤ ይህ ውድ የሆኑ ባህላዊ መድሀኒቶቻቸውንና ሌሎች ነገሮችን ለመሸጥ የሚጠቀሙበት ብልጠት ነው፡፡ አስታውስ፣ እውነት መሆኑ ጥሩ ቢሆንም፤ እውነት ሆኖ ላይገኝ ይችላል፡፡

ስለፆች እና ሌሎች ተያያዥ መድሀኒቶች ተዓማኒ የመረጃ ምንጮች ከዚህ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡ ይህ መረጃ የተመሰረተው በሳይንሳዊ መረጃ ነው፣ በውሸት ቃል አይደለም፡፡ እርግጠኛ ሁን ዋነኛ ግብአቶቹ የምትጠቀምባቸው ባህላዊ መድሀኒቶችና ሌሎች ነገሮች ትክክለኛ እና ጉበትን የማይጎዱ ስለመሆናቸው፡፡ ዋናውና ጠቃሚው ነገር ጉበትህን ከሌላ ማንኛውም ጉዳት መጠበቅ ነው፡፡

የጤናማ ጉበት ምንነት ማሳያዎችይህ ስር ከሰደደ ሄፓታይተስ ቢ ጋር ለሚኖሩ ነው?

ሰር ከሰደደ ሄፓታይተስ ቢ ጋር የሚኖሩ ሰዎች የመድሀኒት ህክምና ሊያስፈልጋቸው ላያስፈልጋቸውም ይችላል፡፡ ነገር ግን ታማሚው ጉበቱን ለመጠበቅ እንዲሁም ጤናውን ለማሻሻል ማድረግ ያለበት ነገሮች ብዙ ናቸው፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ያሉት 10ሩ ጤናማ አማራጮች ዝርዝር ሲሆን ዛሬውኑ መጀመር ያለባቸው ናቸው፡፡

  • የጉበት ስፔሻሊስቱ ወይም የጤና ባለሙያው ጋር አዘውትረው በመሄድ ጤናዎን እንዲሁም የጉበትዎን ጤና ይጠብቁ፡፡
  • ጉበትዎን ከሚያጠቃ ሌላ ቫይረስ ለመጠበቅ የሄፓታይተስ ቢ ክትባትን ይውሰዱ፡፡
  • ቀድሞ በሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ የተጎዳውን ጉበትዎን ከጉዳት ለመጠበቅ አልኮል መጠጣትንና ማጨስ ሁለቱም ጉበትን ስለሚጎዱ ያስወግዱ፡፡
  • የባህል መድሀኒት ወይም ተጨማሪ ቫይታሚኖችን መውሰድ ከመጀመርዎ በፊት ከሀኪምዎ ጋር መነጋገር አለብዎት፤ ምክንያም እነዚህ በሀኪም ከታዘዘልዎት የሄፓታይተስ ቢ መድሀኒት ጋር ስለሚቃረን አሊያም ጉበትን ሊጎዳ ለሚችል ነው፡፡
  • ስለሚቃረኑ መድሀኒቶች እርግጠኛ ለመሆን ፋርማሲስት ጋር ሄዶ ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ (ለምሳሌ አሲታሚኖፌን፣ ፓራሲታሞል) ወይም ለሄፓታይተስ ቢ ያልታዘዙ መድሀኒቶች በጉበት ላይ ምንም ጉዳት ስላለማስከተላቸው እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል፤ ለዚህ ደግሞ ዋናው ምክንያት አብዛኞቹ መደሀኒቶች ጉበት ላይ ሂደታቸውን ጠብቀው ስለሚያልፉ ነው፡፡ 
  • ወደ ውስጣችን ከአየር ጋር የምናስገባቸውን ከቀለም የሚወጡ ሽታዎችን፣ ቀለም ማስለቀቂያ፣ ሙጫ፣ የጥፍር ቀለም ማስለቀቂያ፣ እና ሌሎችም መርዛማ ኬሚካሎች ጉበትን ሊጎዱ ስለሚችሉ መጠንቀቅ ተገቢ ነው፡፡  
  • እንደ ፍራፍሬ፣ ጥራጥሬ፣ አሳ፣ ጮማ ያልበዛበት ስጋ እና በርካታ አታክልት በመጠቀም ጤናማ አመጋገብን መከተል ያስፈልጋል፡፡ “ክሩሲፈረስ አታክልቶች” በተለይም- ጎመን፣ ብሮኮሊ፣ አበባ ጎመን፣ ከአካባቢያዊ ኬሚካል ጉበትን ለመከላከል ይረዳል፡፡ 
  • ጥሬ የሆነና ያልበሰለ አሳን መመገብን አርግፍ አድርጎ መተው ያስፈልጋል (ለምሳሌ ትንንሽ የባህር ውስጥ የአሳ ዝርያዎች መካከል እንደ ክላምስ፣ ሙሴልስ፣ ኦይስተርስ እና ስካሎፕስ የሚባሉት) ምክንያም በባክቴሪያ እንድንበከል ስለሚያደርጉ ቫይበሮ ቩልንፊከስ፣ በጣም መርዛማ በመሆኑ ጉበት ላይ በርካታ ጉዳት ያደርሳል፡፡
  • በእንደ ለውዝ፣ በቆሎ እና ማሽላ ያሉ ምግቦችን ከመጠቀማችን በፊት የሻጋታ ምልክት ስላለመኖሩ እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል፡፡ ሻጋታ በአብዛኛው በምግብ ላይ ችግር የሚሆነው ምግቡ እርጥበት ባለበት ቦታ ላይ ሲቀመጥና በአግባቡ ሳይታሸግ ሲቀር ነው፡፡ ሻጋታ ካለ ምግቡ በ “አፍላቶክሲንስ” የሚበከል ሲሆን ይህ ደግሞ የጉበት ካንሰር የመከሰት እድሉን ከፍ ያደርገዋል፡፡
  • የጭንቀትን መጠን ለመቀነስ ጤናማ አመጋገብን መከተል፣ አዘውትሮ እንቅስቃሴ መስራት እና በቂ እረፍት ማግኘት ተገቢ ነው፡፡ 
  • የምንመገበው፣ የምንጠጣው፣ የምንተነፍሰው ወይም በቆዳችን ወደ ውስጥ የሚገባው ሳይቀር በሂደት በጉበት ማጣራት እንደሚካሄድባቸው ሁሌ ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም ጤናዎን እና ጉበትዎን ይጠብቁ!


ሄፓታይተስ ቢ እያለብኝ ደም መለገስ እችላለሁ?

በጭራሽ፣ የደም ባንክ ለሄፓታይተስ ቢ የተጋለጠን ሰው ደም አይወስድም፤ እንዲያውም በመጀመሪያ ደረጃ ከተያዘና ከተሻለው ሰው እንኳን አይወስድም፡፡

 

 

 

Living with Hepatitis B

Will I recover from a hepatitis B infection?
Most healthy adults who are newly infected will recover without any problems. But babies and young children may not be able to successfully get rid of the virus.

Adults – 90% of healthy adults will get rid of the virus and recover without any problems; 10% will develop chronic hepatitis B. 
Young Children – Up to 50% of young children between 1 and 5 years who are infected will develop a chronic hepatitis B infection.
Infants – 90% will become chronically infected; only 10% will be able to get rid of the virus.


What is the difference between an "acute" and a "chronic" hepatitis B infection?
A hepatitis B infection is considered to be “acute” during the first 6 months after being exposed to the virus. This is the average amount of time it takes to recover from a hepatitis B infection. 
If you still test positive for the hepatitis B virus (HBsAg+) after 6 months, you are considered to have a "chronic" hepatitis B infection, which can last a lifetime.


Will I become sick if I have acute hepatitis B?
Hepatitis B is considered a "silent infection” because it often does not cause any symptoms. Most people feel healthy and do not know they have been infected, which means they can unknowingly pass the virus on to others. Other people may have mild symptoms such as fever, fatigue, joint or muscle pain, or loss of appetite that are mistaken for the flu.

Less common but more serious symptoms include severe nausea and vomiting, yellow eyes and skin (called “jaundice”), and a swollen stomach - these symptoms require immediate medical attention and a person may need to be hospitalized.


How will I know when I have recovered from an "acute" hepatitis B infection?
Once your doctor has confirmed through a blood test that you have gotten rid of the virus from your body and developed the protective antibodies (HBsAb+), you will be protected from any future hepatitis B infection and are no longer contagious to others.


What should I do if I am diagnosed with chronic hepatitis B?
If you test positive for the hepatitis B virus for longer than 6 months, this indicates that you have a chronic hepatitis B infection. You should make an appointment with a hepatologist (liver specialist), gastroenterologist, or family doctor who is familiar with hepatitis B. The doctor will order blood tests and possibly a liver ultrasound to evaluate how active the hepatitis B virus is in your body, and to monitor the health of your liver. Your doctor will probably want to see you at least once or twice a year to monitor your hepatitis B and determine if you would benefit from treatment.
All chronically infected people should be seen by their doctor at least once a year (or more frequently) for regular medical follow-up care, whether they start treatment or not. Even if the virus is in a less active phase with little or no damage occurring, this can change with time, which is why regular monitoring is so important.

Most people chronically infected with hepatitis B can expect to live long, healthy lives. Once you are diagnosed with chronic hepatitis B, the virus may stay in your blood and liver for a lifetime. It is important to know that you can pass the virus along to others, even if you don’t feel sick. This is why it’s so important that you make sure that all close household contacts and sex partners are vaccinated against hepatitis B.

What tests will be used to monitor my hepatitis B?
Common tests used by doctors to monitor your hepatitis B include the hepatitis B blood panel, liver function tests (ALT, AST), hepatitis B e-Antigen (HBeAg), hepatitis B e-Antibody (HBeAb), hepatitis B DNA quantification (viral load), and an imaging study of the liver (ultrasound, FibroScan [Transient Elastography] or CT scan).


Is there a cure for chronic hepatitis B?

Right now, there is no cure for chronic hepatitis B, but the good news is there are treatments that can help slow the progression of liver disease in chronically infected persons by slowing down the virus. If there is less hepatitis B virus being produced, then there is less damage being done to the liver. Sometimes these drugs can even get rid of the virus, although this is not common.

With all of the new exciting research, there is great hope that a cure will be found for chronic hepatitis B in the near future. Visit our Drug Watch for a list of other promising drugs in development.


Are there any approved drugs to treat chronic hepatitis B?

Current treatments for hepatitis B fall into two general categories, antivirals and immune modulators:

Antiviral Drugs - These are drugs that slow down or stop the hepatitis B virus, which reduces the inflammation and damage to the liver. These are taken as a pill once a day for at least 1 year, usually longer. There are 6 U.S. FDA approved antivirals, but only three first-line antivirals are recommended treatments: tenofovir disoproxil (Viread/TDF), tenofovir alafenamide (Vemlidy/TAF) and Entecavir (Baraclude). First-line antivirals are recommended because they are safer and most effective. They also have a better resistance profile than older antivirals, which means that when they are taken as prescribed, there is less chance of mutation and resistance. Building resistance makes it harder to treat and control the virus.

Immunomodulator Drugs - These are drugs that boost the immune system to help control the hepatitis B virus. They are given as injections over 6 months to 1 year. The most commonly prescribed include interferon alfa-2b (Intron A) and pegylated interferon (Pegasys). This is the only recommended treatment for patients coinfected with hepatitis delta.

Do these drugs provide a “cure” for chronic hepatitis B?

Although they do not provide a complete cure, current medications will slow down the virus and decrease the risk of more serious liver disease later in life. This results in patients feeling better within a few months because liver damage from the virus is slowed down, or even reversed in some cases, when taken long-term. Antivirals are not meant to be stopped and started, which is why a thorough evaluation by a knowledgeable doctor is so important before beginning treatment for chronic HBV.


If I have a chronic hepatitis B infection, should I be on medication?
It is important to understand that not every person with chronic hepatitis B needs to be on medication. You should talk to your doctor about whether you are a good candidate for drug therapy. Whether you and your doctor decide you should start treatment or not, you should be seen regularly by a liver specialist or a doctor knowledgeable about hepatitis B.


Is it safe to take herbal remedies or supplements for my hepatitis B infection?
Many people are interested in using herbal remedies or supplements to boost their immune systems and help their livers. The problem is that there is no regulation of companies manufacturing these produces, which means there is no rigorous testing for safety or purity. So, the quality of the herbal remedy or vitamin supplement may be different from bottle to bottle. Also, some herbal remedies could interfere with your prescription drugs for hepatitis B or other conditions; some can even actually damage your liver. These herbal remedies will not cure a chronic hepatitis B infection.

There are many companies that make false promises on the Internet and through social media about their products. Online claims and patient testimonials on Facebook are fake and are used to trick people into buying expensive herbal remedies and supplements. Remember, if it sounds too good to be true, then it’s probably not true.

Below are reliable sources of information about herbs and alternative medicines. This information is based on scientific evidence, not false promises. Check whether the active ingredients in your herbal remedies or supplements are real and safe for your liver. The most important thing is to protect your liver from any additional injury or harm.


What healthy liver tips are there for those living with chronic hepatitis B?
People living with chronic hepatitis B infection may or may not need drug treatment. But there are many other things patients can do to protect their liver and improve their health. Below is our list of the top 10 healthy choices that can be started today!

  • Schedule regular visits with your liver specialist or health care provider to stay on top of your health and the health of your liver.
  • Get the Hepatitis A vaccine to protect yourself from another virus that attacks the liver.
  • Avoid drinking alcohol and smoking since both will hurt your liver, which is already being injured by the hepatitis B virus.
  • Talk to your provider before starting any herbal remedies or vitamin supplements because some could interfere with your prescribed hepatitis B drugs or even damage your liver.
  • Check with your pharmacist about any over-the-counter drugs (e.g. acetaminophen, paracetamol) or non-hepatitis B prescription drugs before taking them to make sure they are safe for your liver since many of these drugs are processed through your liver. 
  • Avoid inhaling fumes from paint, paint thinners, glue, household cleaning products, nail polish removers, and other potentially toxic chemicals that could damage your liver. 
  • Eat a healthy diet of fruit, whole grains, fish and lean meats, and lot of vegetables. “Cruciferous vegetables” in particular -- cabbage, broccoli, cauliflower -- have been shown to help protect the liver against environmental chemicals. 
  • Avoid eating raw or undercooked shellfish (e.g. clams, mussels, oysters, scallops) because they could be contaminated with bacteria called Vibrio vulnificus, which is very toxic to the liver and could cause a lot of damage.
  • Check for signs of mold on nuts, maize, corn, groundnut, sorghum, and millet before using these foods. Mold is more likely to be a problem if food is stored in damp conditions and not properly sealed. If there is mold, then the food could be contaminated by “aflatoxins,” which are a known risk factor for liver cancer.
  • Reduce your stress levels by eating healthy foods, exercising regularly, and getting plenty of rest. 
  • Keep in mind everything you eat, drink, breathe, or absorb through the skin is eventually filtered by the liver. So, protect your liver and your health!


Can I donate blood if I have hepatitis B?
 
No. The blood bank will not accept any blood that has been exposed to hepatitis B, even if you have recovered from an acute infection.