እርግዝና እና ሄፓታይተስ ቢ
ነፍሰጡር ከሆንኩ የሄፓታይተስ ቢ ምርመራ ማድረግ አለብኝ?
አዎ! ሁሉም ነፍሰ ጡር እናቶች የሄፓታይተስ ቢ ምርመራ ማድረግ አለባቸው! ነፍሰ ጡር ከሆንሽ ዶክተርሽ የሄፓታይተስ ቢ ምርመራ እንዳደረገልሽ አርግጠኛ ሁኚበፊት ልጅሽ ከመወለዱ፡፡
እነዚህ ምርመራዎች ለነፍሰጡር እናቶች በጣም አስፈላጊ የሆኑት ለምንድን ነው?
የሄፓታይተስ ቢ ምርመራ ውጤትሽ ፖዘቲቭ ሆኖ ነፍሰጡር ከሆንሽ፤ ቫይረሱ በእርግዝና እና በወሊድ ግዜ አዲስ ወደሚወለደው ህፃን ይተላለፋል፡፡ ሄፓታይተስ ቢ እንዳለብሽ ዶክተሩ ካወቀ በማዋለጃ ክፍል ውስጥ ወደ ልጅሽ እንዳይተላለፍ ተገቢ የሆነ ህክምና ሊያደርግልሽ ይገባል፡፡ ተገቢውን ሂደት መከተል ካልተቻለ ልጅሽ ስር በሰደደው ሄፓታይተስ ቢ የመያዝ እድሉ እስከ 95% ነው፡፡
በሄፓታይተስ ቢ መያዝ በእርግዝናዬ ላይ ተፅዕኖ ያመጣል?
በእርግዝና ወቅት የሄፓታይተስ ቢ ኢንፌክሽን በአንቺና እና ባልተወለደው ልጅሽ ላይ ምንም ችግር ማስከተል የለበትም፡፡ አንቺ በሄፓታይተስ ቢ ስለመያዝሽ ዶክተርሽ ሊውቅ ይገባል፤ ይህን ተከትሎም ዶክተሩ በጤናሽ ላይ በሚያደርገው ክትትል ልጁ ከተወለደ በኋላ እንዳይያዝ ለማድረግ ያስችላል፡፡
እኔ ነፍሰጡር ብሆንና ሄፓታይተስ ቢ ቢኖርብኝ፣ እንዴት ነው ልጄን መጠበቅ የምችለው?
የሄፓታይተስ ቢ ውጤትህ ፖዘቲቭ ከሆነ ዶክተርህ ለሄፓታይተስ ቢ e-antigen (HBeAg) ምርመራ የሚያደርግልህ ይሆናል፤ ከዚህ በተጨማሪም ፖዘቲቭ ሆነህ የሄፓታይተስ ቢ ቫይራል ሎድ ብለድ ቴስት (HBV DNA quantification) ምርመራም የሚደረግልህ ይሆናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የላቦራቶሪ ውጤት ከፍተኛ የቫይራል ሎድ መኖሩን ያሳያል፡፡ ሀኪምዎ በመጨረሻዎቹ ሶስት ወራት አካባቢ በአፍ የሚሰጥ የአንቲቫይራል መድሀኒት እንዲጠቀሙ ይመክራል፤ ይህም በወሊድ ግዜ አዲስ የሚወለደው ህፃን እንዳይያዝ ያደርገዋል፡፡
ሄፓታይተስ ቢ እንዳለብዎ ከታወቀ፣ አዲስ የተወለደው ልጅዎ በማዋለጃ ክፍል ውስጥ እንዳለ ወዲያውኑ ሁለት ክትባት ሊሰጠው ይገባል፡፡
- የመጀመሪያው ክትባት የሄፓታይተስ ቢ ክትባት
- አንዱ ክትባት ሄፓታይተስ ቢ ኢሚዩኖ ግሎቡሊን (HBIG)
በመጀመሪያዎቹ 12 ሰዓታት ውስጥ እነዚህ ሁለቱ መድሀኒቶች በትክክል ቢሰጡ፣ አዲስ የተወለደው ህፃና እድሜ ዘመኑን አብሮት ሊኖር ከሚችለው የሄፓታይተስ ቢ ከ90% በላይ ተጠብቆ የመኖር እድል አለው፡፡
ቀሪዎቹን ከ2-3 የሚደርሱ የሄፓታይተስ ቢ ክትባቶች በመርሀግብሩ መሰረት ልጅዎ ስለመውሰዱ እርግጠኛ መሆን አለብዎት፡፡ ጨቅላ ልጅዎን ሙሉ በሙሉ ከሄፓታይተስ ቢ ለመጠበቅ ሁሉንም ክትባቶች ማስከተብ ያስፈልጋል፡፡ ሄፓታይተስ ቢ ካለባት እናት የተወለደ ልጅ የፖስት ቫክሲኔሽን ሰሮሎጂክ ምርመራ ከ9-12 ወራት ውስጥ በማድረግ ህፃኑ ከሄፓታይተስ ቢ መጠበቁንና አለመያዙን ማረጋገጥ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ምርመራው HBsAg እና anti-HBs titer ምርመራን ያካትታል፡፡
አዲስ የሚወለደውን ህፃን ለመጠበቅ የሚያስችል ሌላ ሁለተኛ እድል የለም!
ክትባቱ ከዩናይትስቴትስ ውጭ
በአብዛኞቹ ሀገሮች ፔንታቫለንት የሚባሉት ክትባቶች 5ቱን በአንድ ክትባት አጣምረው የያዙና አምስት አይነት በሽታዎችን ለመከላከል (ዲፕቴሪያ፣ ፐርቱሲስ፣ ቲታነስ፣ ሂብ እና ሄፓታይተስ ቢ) የሚረዱ ሲሆኑ 6ሳምንት ካለፈው ህፃን ጀምሮ እስከ 1 ዓመት ያሉት ሊወስዱት ይችላሉ፡፡ የመጀመሪያው ክትባት የሚሰጠው በ6 ሳምንት ሲሆን ሁለተኛው እና ሶስተኛው ክትባቶች ደግሞ የሚሰጡት በ10 እና በ14ኛው ሳምንት እድሜ ነው፡፡ ፔንታቫለንት ክትባቶች የሚሰጡት በነፃ ሲሆን ለዚህም ድጋፍ ያደረገው ጋቪ፣ የክትባት ጥምረት፡፡ ጋቪ ያለባቸውን ሀገራት ተመልከት፤ ያለውን ሀብት እና ኢሙዩናይዜሽን ለማየት፦ http://www.gavi.org/country/፡፡
ሄፓታይተስ ቢ ካለባት እናት የተወለደ ህፃን የመጀመሪውን የፐተንታቫለንት ክትባት የሚጠብቅ ከሆነ ከመዘግየትም ባለፈ በወሊድ ወቅት እንዲሁም በመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ከመያዝ አይድንም፡፡ ሄፓታይተስ ቢ ያለባት ሴት ቫይረሱን ወደልጅዋ በማስተላለፍ ስርለሰደደ በሽታ ታጋልጠዋለች፡፡
አለም አቀፉ የጤና ድርጅት ሁሉም ህፃናት በተወለዱ 24 ሰዓት ውስጥ ሄፓታይተስ ቢ ክትባት መከተብ እንዳለባቸው ይመክራል፡፡ አርቀው ያቅዱ እና በመጀመሪያ ስለሚወሰደው ነጠላ ክትባት መኖርና ዋጋ ይጠይቁ፣ ስለ ክትባቱ መጠን ያስቡ፤ ይህ በጋቪ ድርጅት እንደሚቀርበው ዓይነት በሽታን ለመከላል የሚያስችል አይደለም፡፡ ይህ በተለይም በሄፓታይተስ ቢ ለተያዙ እናቶች ጠቃሚ ነው፡፡
እርስዎ ምናልባት ስለ ሄፓታይተስ ቢ እርግጠኛ መሆን ካልቻሉ ዶክተርዎ የሄፓታይተስ ቢ ምርመራ ሊያደርግልዎት ይገባል፡፡
የፔንታቫላንትን ክትባት ያልወሰዱ ህፃናት፣ የመጀመሪያውን የሞኖቫላንት ሄፓታይተስ ቢ ክትባት ህፃኑ በተወለደ የመጀመሪያዎቹ 12 ሰዓታት ውስጥ የግድ ሊሰጠው የሚገባ ሲሆን ቀሪዎቹ ከ2-3 የሚደርሱት ክትባቶች ደግሞ በተያዘላቸው መርሀ ግብር መሰረት መሰጠት አለባቸው፡፡
የፔንታቫላንትን ክትባትን እየወሰዱ ያሉ ህፃናት፣ ለሄፓታይተስ ቢ የሚሰጠውን የመጀመሪያውን የሞኖቫለንት ክትባት በተወለዱ በ12 ሰዓት ውስጥ ሊሰጣቸው የሚገባ ሲሆን የሄፓታይተስ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ክትባት በፔንታቫላንት 1ኛ እና 2ኛ ክትባት ውስጥ የሚካተት ይሆናል፡፡
*ማስታወሻ፦ ሲዲሲ የሄፓታይተስ ቢ የመጀመሪያ ክትባትን እና HBIG በመጀመሪያዎቹ 12 ሰዓታት ውስጥ ሁለቱም ሊሰጡ እንደሚገባ ይመክራል፡፡ HBIG በሁሉም ሀገራት ላይኖር ይችላል፡፡
በእርግዝናዬ ጊዜ ህክምና ያስፈልገኛል?
በእርግዝና ወቅት የሄፓታይተስ ቢ ኢንፌክሽን በአንቺና እና ባልተወለደው ልጅሽ ላይ ምንም ችግር ማስከተል የለበትም፡፡ አንቺ በሄፓታይተስ ቢ ስለመያዝሽ ዶክተርሽ ሊውቅ ይገባል፤ ይህን ተከትሎም ዶክተሩ በጤናሽ ላይ በሚያደርገው ክትትል ልጁ ከተወለደ በኋላ እንዳይያዝ ለማድረግ ያስችላል፡፡ የምትኖረው ከአሜሪካ ውጭ ከሆነ እና ሄፓታይተስ ቢ እንዳለብህና እንደሌለብህ እርግጠኛ መሆን ካልቻልክ ዶክተርህን በማናገር የሄፓታይተስ ቢ ምርመራ ማድረግ አለብህ፡፡
ህፃናት ሲወለዱ የተከተቡት የሄፓታይተስ ቢ ክትባትውጤት አለማምጣት እና HBIGበሴቶች ላይ ምናልባትምHBeAg ፖዘቲቭ በሆኑ እና የቫይራል ሎዳቸው በጣም ከፍ ባሉት ላይ ሄፓታይተስ ቢ ወደ ሰውነታችን እንዲተላለፍ ይሆናል፡፡
ሄፓታይተስ ቢ እንዳለባቸው የታወቀላቸው ሁሉም ነፍሰጡር እናቶች ክትትል እንዲደረግላቸው በሄፓታይተስ ቢ ላይ ብቃት ወዳለው የህክምና ባለሙያ መላክ አለባቸው፡፡ ሀኪምዎ እንደ ሄፓታይተስ ቢ e-antigen፣ HBV DNA level፣ እና ጉበት መስራቱን የሚያረጋግጥ ምርመራዎች (ALT) ያሉ ተጨማሪ የላቦራቶሪ ምርመራዎችን ማድረግ አለበት፡፡
የቫይረሱ ሌቭል ከ200,000 IU/mL ወይም 1 million cp/mlከበለጠ የሚያሳየው ሲወለድ የተከተበው ክትባት መጠን እና HBIGጥምረት ዝቅ ማለቱን ነው፡፡ ከወሊድ በፊት የመጀመሪያ የአንቲቫይራል ቴራፒ ከቴኖፎቪር ጋር የቫይራል ሎዱን ለመቀነስ ይመከራሉ፡፡ ቴኖፎቪር ለነፍሰጡር እና ጡት ለሚያጠቡ እናቶች አስተማማኝ መሆኑ ታይቷል፡፡ ምናልባት ቲኖፎቪር ውጤታማ ካልሆነ ዶክተሮቹ ቴልቢቩዲን ወይንም ላሚቩዲንን ሊያዙ ይችላሉ፡፡ የአንቲቫይራል ትሪትመንት ከ 28-32 ሳምንታት ውስጥ ጀምሮ እስከ 3 ወር ያለማቋረጥ ይቀጥላል፡፡
ከእርግዝናዬ በኋላ የህክምና ክትትል ያስፈልገኛል?
በእርግዝናዎ ወቅት አንቲቫይራል እንዲወስዱ ከታዘዙ፣ ከ3 እስከ 6 ወር አንድ ጊዜ በALT (SGPT) መታየት አለብዎት፡፡ ይህ የአንቲቫይራል ህክምናውን መቀጠል እንዳለብዎት ለመወሰን ይረዳል፡፡ እባክዎ በውጤትዎ መሰረት የታዘዘልዎትን የአንቲቫይራል መድሀኒት ዶክተርዎ ካላዘዝውት በቀር እንዳያቋርጡ፡፡ ለአብዛኞቹ ሴቶች የክትትል ውጤታቸው ምንም አይነት በሽታ አለመኖሩን ሲያሳይ፤ የእርስዎ ሀኪም፣ ጉበት ስፔሻሊስት ጋር ክትትል እንዲያደርጉ ይመክራሉ፡፡
ሁሌም አዋላጅ ሀኪምዎ እና አዲስ የተወለደው ልጅዎ ሀኪም ስለ እርስዎ የሄፓታይተስ ቢ ደረጃ ማወቃቸው ልጅዎ በቀጣይ ዘመኑ ሄፓታይተስ ቢ እንዳይኖርበት ለማድረግ ክትባት እንዲወስድ ሲያግዝ እርስዎ ደግሞ ተገቢውን የህክምና ክትትል እንዲገኙ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡
ሄፓታይተስ ቢ ቢኖርብኝ ልጄን ጡት ማጥባት እችላለሁ?
ጡት ማጥባት የመያዝ እድልን ይቀንሳል፣ ምንም እንኳን ዝቅ ያለ ቢሆንም፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ህጻናት ሲወለዱ ሄፓታይተስ ቢ ን ለመከላከል የሚያግዘውን ክትባት መከተባቸው የሚመከርና በቀጣይ ሊመጣ የሚችልን ማንኛውም አይነት ችግር የመቀነስ እድልን ይፈጥራል፡፡ ለሄፓታይተስ ቢ ተብሎ የሚታዘዘው ቲኖፎቪር ጡት ለሚያጠቡ እናቶች አስተማማኝ ስለመሆኑ የሚያሳይ መረጃ አለ፡፡
Pregnancy and Hepatitis B
Should I be tested for hepatitis B if I am pregnant?
Yes, ALL pregnant women should be tested for hepatitis B! If you are pregnant, be sure your doctor tests you for hepatitis B before your baby is born.
Why are these tests so important for pregnant women?
If you test positive for hepatitis B and are pregnant, the virus can be passed on to your newborn baby during your pregnancy or during delivery. If your doctor is aware that you have hepatitis B, he or she can make arrangements to have the proper medications in the delivery room to prevent your baby from being infected. If the proper procedures are not followed, your baby has a 95% chance of developing chronic hepatitis B!
Will a hepatitis B infection affect my pregnancy?
A hepatitis B infection should not cause any problems for you or your unborn baby during your pregnancy. It is important for your doctor to be aware of your hepatitis B infection so that he or she can monitor your health and so your baby can be protected from an infection after it is born.
If I am pregnant and have hepatitis B, how can I protect my baby?
If you test positive for hepatitis B, your doctor should also test you for the hepatitis B e-antigen (HBeAg), and if positive, you should have a hepatitis B viral load blood test (HBV DNA quantification). In some cases, the laboratory test results may show a very high viral load. In these cases, your physician may recommend that you take an oral antiviral drug in the third trimester, which is safe to take to reduce the risk of infecting your newborn at birth.
If you test positive for hepatitis B, then your newborn must be given two shots immediately in the delivery room:
First dose of the hepatitis B vaccine
One dose of hepatitis B immune globulin (HBIG)
If these two medications are given correctly within the first 12 hours of life, a newborn has more than a 90% chance of being protected against a lifelong hepatitis B infection.
You must make sure your baby receives the remaining 2-3 doses of the hepatitis B vaccine according to schedule. All doses must be completed in order for your infant to be fully protected against hepatitis B. It is also important that a baby born to an HBV-positive mother receive post-vaccination serologic testing at 9-12 months to confirm the baby is protected against HBV and is not infected. Tests include the HBsAg and anti-HBs titer test.
There is no second chance to protect your newborn baby!
Vaccination Outside the United States
In many countries, the pentavalent vaccine, a combination 5-in-one vaccine that protects against five diseases (diphtheria, pertussis, tetanus, Hib and hepatitis B) may be given to babies more than 6 weeks of age and can be given up to 1 year of age. The first dose is given at 6 weeks, and the second and third doses are given at 10 and 14 weeks of age. The pentavalent vaccine may be made available free of charge with the support of Gavi, the Vaccine Alliance. Check the Gavi country hub to see the resources and immunizations that may be available: http://www.gavi.org/country/.
For babies born to mothers with hepatitis B, waiting for the first dose of the pentavalent vaccine is too late and will NOT protect the baby from becoming infected during birth or within the first six weeks of life. A woman who is hepatitis B positive is likely to pass the virus on to her baby, who will then be chronically infected.
WHO recommends the hepatitis B vaccine within 24 hours of birth for ALL babies. Plan ahead and inquire about the availability and cost of the monovalent (single), birth dose of the vaccine, as it is not a Gavi provided immunization. This is particularly important to women who are positive for hepatitis B.
If you are unsure of your hepatitis B status, please be sure your doctor tests you for hepatitis B!
For babies NOT receiving the pentavalent vaccine, the first dose of the monovalent, HBV vaccine must be given within 12 hours of birth, followed by the remaining 2-3 doses of the hepatitis B vaccine according to schedule.
For babies receiving the pentavalent vaccine, the first, monovalent dose of the hepatitis B vaccine is given within 12 hours of birth, and the second and third doses of the HBV vaccine will be included in dose 1 and dose 2 of the pentavalent vaccine.
*Note: CDC recommends both the first shot of the HBV vaccine and HBIG within 12 hours of birth. HBIG may not be available in all countries.
Do I need treatment during my pregnancy?
A hepatitis B infection should not cause any problems for you or your unborn baby during your pregnancy. It is important for your doctor to be aware of your hepatitis B infection so that he or she can monitor your health and so your baby can be protected from an infection after it is born. If you live outside of the U.S. and are unsure of your hepatitis B status, please ask your doctor to test you for hepatitis B.
Failure of the birth dose of the HBV vaccine and HBIG may occur in women who are HBeAg positive and have a very high viral load, allowing for the transmission of hepatitis B to your baby.
All women who are diagnosed with hepatitis B in pregnancy should be referred for follow up care with a physician skilled at managing hepatitis B infection. Your physician should perform additional laboratory testing, including hepatitis B e-antigen, HBV DNA level, and liver function tests (ALT).
A virus level greater than 200,000 IU/mL or 1 million cp/ml indicates a level where the combination of the birth dose of the vaccine and HBIG may fail. First-line, antiviral therapy with tenofovir may be recommended to reduce the viral load prior to birth. Tenofovir has been shown to be safe both during pregnancy and for breastfeeding mothers. In cases where tenofovir is not effective, doctors may prescribe telbivudine or lamivudine. Antiviral treatment begins at 28-32 weeks and continues 3 months postpartum.
Do I need treatment after my pregnancy?
If you are prescribed antivirals during pregnancy, you should have your ALT (SGPT) monitored every 3 months for 6 months. This will help determine if you should continue antiviral treatment. Please do not discontinue your antiviral medication unless the doctor advises you to, based upon test results. For most women whose follow up testing shows no signs of active disease, your physician will recommend regular monitoring with a liver specialist.
In all cases, it is very important that your obstetrician and your newborn’s pediatrician, are aware of your hepatitis B status to ensure that your newborn receives the proper vaccines at birth to prevent a lifelong hepatitis B infection, and that you receive appropriate follow up care.
Can I breastfeed my baby if I have hepatitis B?
The benefits of breastfeeding outweigh the potential risk of infection, which is minimal. In addition, since it is recommended that all infants be vaccinated against hepatitis B at birth, any potential risk is further reduced. There is data that shows that tenofovir, which may be prescribed to manage hepatitis B, is safe for breastfeeding women.